እንኳን ወደ ፍትህ ሚኒስቴር በደህና መጡ

“ለሕግ፣ ለፍትህ፣ ለርትዕ”

ጀምር

የክብርት ሚኒስትሯ መልክት

የፍትህ ሚኒስትሯ ክብርት ወ/ሮ ሐና አርያስላሴ መልዕክት

  • ፍትህ ሚኒስቴር የሀገራችን የዴሞክራሲና ፍትህ መሰፈን፣ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲሁም የህዝቡ የላቀ ተጠቃሚነት ያለ ሕግ የበላይነትና የፍትህ ዘርፍ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ የአገራችን የፍትህ ዘርፍ ታሪክ ስር በሰደዱ አናቂ የሕግና የአሰራር እንዲሁም የአመለካካት ችግሮች የተተበተበ እና የጉልበተኞች ምርኮኛ እንደነበር ይታወሳል፡፡
  • በተጀመረው አዲስ የለውጥ ምዕራፍ ተቋማችን የሕግ እና ፍትህ ሪፎርም በማከናወን እንዲሁም የአሰራር ችግሮችን በማሻሻል፣ ከሰብአዊ መብት አኳያ የሕግ ታራሚዎችን አያያዝ በማስተካከል ተቋማዊ አግልግሎትን ቀልጣፋ፣ ፍትሀዊና ውጤታማ የሆኑ የፍትህ ተደራሽነትን በማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ መሠረታዊ የለውጥ ተግባራትን አከናውኗል፣በማከናወን ላይም ይገኛል፡፡
  • ፍትህ ሚኒስቴር በአገራዊ የለውጥ ጉዞ ዳር ለማድረስ በሚደረገው ሰፊና ሁለንተናዊ ርብርብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በአዋጅ ቁጥር 943/2008 በተሰጠው ስልጣን የፍትህ እና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማክበርና ማስከበር፣ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ ፍትህን በማስፈን፣ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲረጋገጡ ሀገራዊ ተልዕኮውን ከመቸውም ጊዜ በላቀ ደረጃ በመወጣት ላይ ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...

ራዕይ፣ተልዕኮና እሴቶች

ራዕይ

በ2022 የአፍሪካ የፍትሕ ተቋማት ተምሳሌት ሆኖ ማየት

ተልዕኮ

የህግ የበላይነትንና ሰብዓዊ መብትን በማክበርና በማስከበር፤ ወንጀልን በመከላከል፣ ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥና የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም በማስጠበቅ፤ የሕዝብ ዓመኔታ ያተረፈ ተደራሽ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት መስጠት፡፡

እሴቶች

ሰብዓዊ ክብር የሕግ የበላይነት ታማኝነት ተጠያቂነትና ግልጽነት ሙያዊ ብቃት/ፕሮፌሽናሊዝም/ ትብብርና አጋርነት ፍትሐዊነት

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

የኮንትራት ድርድር

ግዙፍ የመንግስት ፕሮጀክቶችን ጨምሮ እንደ ግንባታ፣ የእቃ ወይም ምክርን ጨምሮ የአገልግሎት ግዥ ወይም ሌሎች ውሎችን ... በተመለከተ የተዘጋጁ ረቂቆች እንዲመረመሩ ለማድረግ ወይም ለአንድ ግዢ ለሚከናወንበት ጉዳይ ወይም በግዢ ህጉ መሰረት ለሚሰጥ ስራ ረቂቅ ስምምነት እንዲዘጋጅ ለሚቀርብ ጉዳይ የሚሰጥ አገልግሎት ሲሆን ከውሉ መፈረም አስቀድሞ በሚደረግ የውል ድርድር ተሳትፎ ለማድረግ የሚጠየቅ አገልግሎትን ይጨምራል፡፡

የህግ ምክር

ፍትህ ሚኒስቴር በሕግ ጉዳዮች የፌዴራል መንግስትን የማማከር ኃላፊነት በህግ ተሰጥቶታል። ይህን መነሻ በማድረግ ለመንግስት ተቋማት የህግ ምክር አገልግሎት ... በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን በረቂቅ ህግ ዝግጅት፣ በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ህግ ነክ ችግሮች እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ምክር/አስተያየት የሚሰጥበት ሂደት ነው። የህግ ምክር አገልግሎት ለማግኘት ምክር የሚፈለግበት ጉዳይ ዝርዝር እና የጉዳዩ አመጣጥ በአግባቡ ተብራርቶ፣ በተቋሙ የስራ ኃላፊ ተፈርሞ እና የተቋሙ ማህተም የተደረገበት ደብዳቤ መቅረብ አስፈላጊ ነው።

የፍትሓ ብሔር የህግ ምክር

ከውል ስምምነት ወይም ከውል ውጪ ኃላፊነት ወይም አማራጭ አለመግባባት መፍቻ ዘዴዎችን በተመለከተ ወይም በዳኝነት አካላት ... በቀረቡ ወይም ሌሎች ህግ ነክ የፍትሐብሄር ጉዳዮችን በተመለከተ በፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የልማት ድርጅቶች ወይም የገንዘብ አቅም በሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የሚጠየቅ የህግ አስተያየት ወይም የጉዳይ አመራር አቅጣጫ ነው፡፡

የሕግ ማርቀቅ

ለፍትህ ሚኒስቴር በህግ ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል የሕግ ማርቀቅ ወይም የህግ ረቂቅ ማዘጋጀት አገልግሎት አንዱ ሲሆን በሕግ ጥናት፣ ማርቀቅ እና ማጠቃለል ... ዳሬክቶሬት ጄኔራል የሥራ ክፍል የሚከናወን ነው። የሚረቀቀውም ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ህግ (አዋጅ፣ ደንብ ወይም መመሪያ) ሊሆን ይችላል። በፍትሕ ሚኒስቴር ሕግ እንዲረቀቅላቸው የሚፈልጉ የመንግስት ተቋማት አገልግሎቱን ለማግኘት የሕግ ይረቀቅልኝ ጉዳይ ማቅረብ፣ በጉዳዩ ላይ የተዘጋጀ ፖሊሲ ሰነድ ካለ፣ በጉዳዩ ላይ የተደረገ የጥናት ሰነድ እንዲሁም ማሻሻያ ረቂቅ ህግ የሚዘጋጅ ከሆነ የሚሻሻለው ሕግ ቁጥር ወይም የሚረቀቀው ሕግ ደንብ ወይም መመሪያ ከሆነ እናት ሕጉ (ደንብ ወይም መመሪያውን እንዲወጣ ሥልጣን የሚሰጠው አዋጅ ቁጥር) ጠቅሶ ማሳወቅ እንደ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጠዋል።

አስገዳጅ ውሳኔ መስጠት፡

የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ በርሳቸው ባልተግባቡበት የፍትሐብሔር ጉዳይ ላይ በአዋጅ ቁጥር 1263/2021 አንቀጽ 40(2)(ሀ) ... መሰረት ውሳኔ እንዲሰጥ የሚቀርብ ጉዳይ ነው፡፡

የህግ ማረም

የህግ ማረም አገልግሎት በመንግስት ተቋማት የተዘጋጀውን ረቂቅ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ህግ (አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ) ከህገ መንግስቱ፣ ሀገራችን ከተቀበለቻቸው ... ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ ሌሎች ብሔራዊ ህጎች ጋር ተጣጥሞ የተዘጋጀ መሆኑን እና የህግ ማርቀቅ መርሆችን የተከተለ መሆኑን ለማረጋገጥ በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ስራ ክፍል የሚከናወን የረቂቅ ምርመራ እና አስተያየት ዝግጅት ስራ ነው። የህግ እርማት ጉዳይ ሲቀርብ በጉዳዩ ላይ የተዘጋጀ ፖሊሲ፣ በጉዳዩ ላይ የተደረገ መነሻ ጥናት፣ የረቂቅ ሕጉ የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቅጂ እንዲሁም የረቂቅ ህጉ ማብራሪያ በዎርድ ፎርማት በሶፍት ኮፒ እና በሃርድ ኮፒ ማቅረብ ከአገልግሎት ጠያቂው የመንግስት ተቋም ይጠበቃል።

ዓለም አቀፍ ጉዳዮች

የፌዴራል መንግሥት ወይም ተቋማት በውጭ ሀገር የገጠማቸውን ክስ ወይም ንግድ ነክ አለመግባባት አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥ ወይም ድርድር ... ላይ ተሳትፎ እንዲደረግ ወይም በዳኝነት አካላት ክርክር እንዲደረግ ወይም ማናቸውም ከአለም አቀፍ ፍትሐብሄር ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተቋማት የሚቀርብ የድጋፍ ጉዳይ ነው፡፡

የመመሪያ ምዝገባ

መመሪያ ሕግ አውጪው አካል በሚሰጠው የውክልና ስልጣን መሰረት በአስተዳደር ተቋም የሚወጣና የተቋሙን ስራ ለማቀላጠፍ የሚያስችል የሕግ ሰነድ ነው። ... የሚዘጋጀው መመሪያ አዲስ፣ በስራ ላይ ያለ መመሪያን የሚያሻሻል ወይም የሚሽር ሊሆን ይችላል። በአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 መሰረት ፍትህ ሚኒስቴር በመንግስት ተቋማት የሚዘጋጁ መመሪያዎችን መዝግቦ ቁጥር በመስጠት ለተደራሽነት በመስሪያ ቤቱ ድረ ገፅ ላይ የመጫን ኃላፊነት ተሰጥቶታል። በተቋማት የሚዘጋጁ መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ከሕዝብ እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ፣ ረቂቅ መመሪያውን ለፍትህ ሚኒስቴር አቅርቦ አስተያየት እንዲሰጥበት ማድረግ ይጠበቃል። ይህን ሂደት አልፎ ለምዝገባ የሚላክ መመሪያ በተደረጉት ውይይቶች እና በተሰጡት አስተያየቶች መሰረት ማስተካከያ የተደረገበት እና የአርትኦት ስራ የተሰራበት፣ መመሪያው በአማርኛ እና በኢንግሊዝኛ ቅጂ የተዘጋጀ፣ የመመሪያው ማብራሪያ፣ መመሪያው በአዘጋጅ ተቋሙ በሚመለከተው አካል (ስራ አመራር) የፀደቀ መሆኑን የሚያሳይ ደብዳቤ ተያይዞ መቅረብ አለበት። እነዚህ ሰነዶች በሀርድ ኮፒ እና በሶፍት ኮፒ (በሲዲ) መላክ አለባቸው።

ክርክር

የፌዴራል የመንግስት ተቋማት ወይም የገንዘብ አቅም የሌላቸው ዜጎች የገጠማቸውን የፍትሐብሔር ወይም ንግድ ነክ የመብትና ጥቅም ጉዳይ በተለይ ለፌዴራል ... ፍርድ ቤት ወይም ለሌላ የዳኝነት አካል ክስ አቤቱታ እንዲቀርብ፣ ለአቤቱታዎች ምላሽ እንዲሰጥ፣ ወይም እግድና ይግባኝ እንዲቀርብ እንደ አግባብነቱ በጋራ ወይም በተናጠል ክርክር ለማድረግ የሚጠየቅ አገልግሎት ነው፡፡

ምርመራ እና ክትትል

ሁሉም የመንግስት ተቋማት የሚገቡትን ውል እና የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ተፈጥሮ ምንም ይሁን ምን መረጃ እንዲሰጡ በሕግ ይገደዳሉ። ስለዚህ ጉዳያቸው ምን ያህል ... እንደሆነ ለማወቅና የህዝብን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ በተቋማቱ በአግባቡ እየተስተናገዱ መሆኑን ለመፈተሽ ሲኢአድጂ የመንግስት ተቋማትን በአካል ይጎበኛል። በግኝቶቹ መሰረት፣ CJADG ምክሮችን ይሰጣል እና የውሳኔ ሃሳቦቹን አፈፃፀም ይከታተላል። የመረጣቸውን ጉዳዮች በቀጥታ በማስተናገድ ላይም ይሠራል።

አማራጭ የአለመግባባት መፍቻ ዘዴዎች

የመንግሥት ተቋማት እርስ በርስ ወይም የመንግሥት ተቋማት ከግለሰቦች ወይም የግል ድርጅቶች የሚኖራቸውን ንግድ ነክና ፍትሐብሔር ... አለመግባባት በድርድር፣ በስምምነት፣ በዕርቅ ወይም በሌላ ከፍርድ ቤት ውጭ ባለ አማራጭ እንዲፈታ ለማድረግ ወይም አቅመ ደካማ የሆኑ ዜጎች አለመግባባታቸውን ከፍርድ ቤት ውጭ ባለ አማራጭ እንዲፈታላቸው የሚቀርብ አገልግሎት ሲሆን በድርድር፣ የግልግል ዳኝነትና የፍርድ ቤት ወይም ከፊል የዳኝነት አካል በተጀመረ ሂደት ላይ እገዛ እንዲደረግ የሚቀርብ ጉዳይ ን ያካትታል፡፡

ምክረ-ሀሳብ

መመሪያ ሕግ አውጪው አካል በሚሰጠው የውክልና ስልጣን መሰረት በአስተዳደር ተቋም የሚወጣና የተቋሙን ስራ ለማቀላጠፍ የሚያስችል የሕግ ሰነድ ነው። የሚዘጋጀው ... መመሪያ አዲስ፣ በስራ ላይ ያለ መመሪያን የሚያሻሻል ወይም የሚሽር ሊሆን ይችላል። በአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 መሰረት ፍትህ ሚኒስቴር በመንግስት ተቋማት የሚዘጋጁ መመሪያዎችን መዝግቦ ቁጥር በመስጠት ለተደራሽነት በመስሪያ ቤቱ ድረ ገፅ ላይ የመጫን ኃላፊነት ተሰጥቶታል። በተቋማት የሚዘጋጁ መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ከሕዝብ እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ፣ ረቂቅ መመሪያውን ለፍትህ ሚኒስቴር አቅርቦ አስተያየት እንዲሰጥበት ማድረግ ይጠበቃል። ይህን ሂደት አልፎ ለምዝገባ የሚላክ መመሪያ በተደረጉት ውይይቶች እና በተሰጡት አስተያየቶች መሰረት ማስተካከያ የተደረገበት እና የአርትኦት ስራ የተሰራበት፣ መመሪያው በአማርኛ እና በኢንግሊዝኛ ቅጂ የተዘጋጀ፣ የመመሪያው ማብራሪያ፣ መመሪያው በአዘጋጅ ተቋሙ በሚመለከተው አካል (ስራ አመራር) የፀደቀ መሆኑን የሚያሳይ ደብዳቤ ተያይዞ መቅረብ አለበት። እነዚህ ሰነዶች በሀርድ ኮፒ እና በሶፍት ኮፒ (በሲዲ) መላክ አለባቸው።

“ለሕግ፣ ለፍትህ፣ ለርትዕ”

አግኙን

አግኙን

አድራሻችን

Bambis, Jomo Kenyatta Avenue,Addis Ababa, Ethiopia

ኢ_ሜይል

info@mog.gov.et

ይደውሉልን

011 551 5099