Message from the Honorable Minister
The message of the Honorable Minister of Justice, Hanna Arayaselassie Zemichael
- Ministry of Justice: Our country's democracy and justice, rapid and continuous development, and the people's greater benefit cannot be ensured without the rule of law and the practical activities of the justice sector. It will be remembered that the history of our country's justice sector has been plagued by deep-rooted problems of law and procedure as well as attitudes and was a captive of bullies.
- In the new phase of change that has started, our institution has carried out, and is still carrying out, many basic reform activities by carrying out law and justice reform and improving operational problems, by adjusting the treatment of legal prisoners in terms of human rights, ensuring efficient, fair and effective access to justice in institutional services.
- The Ministry of Justice is carrying out its national mission at a higher level than ever before by creating a favorable environment for wide and universal cooperation to bring about the national journey of change, respecting and enforcing the judicial and constitutional system, ensuring the rule of law, ensuring justice, and ensuring the human and democratic rights of citizens. .
The vision, mission and values of the Ministry of Justice of the Federal Democratic Repablic of Ethiopia
In 2022, seeing it as a model of African justice institutions
Respecting and upholding the rule of law and human rights; By preventing crime, ensuring peace and security and protecting the interests of the government and the people; Providing accessible, efficient, fair and effective justice services that have won public disapproval.
Human dignity The rule of law Loyalty Accountability and transparency Professionalism Cooperation and partnership Justice
Our Services
Contract Negotation
ግዙፍ የመንግስት ፕሮጀክቶችን ጨምሮ እንደ ግንባታ፣ የእቃ ወይም ምክርን ጨምሮ የአገልግሎት ግዥ ወይም ሌሎች ውሎችን ...በተመለከተ የተዘጋጁ ረቂቆች እንዲመረመሩ ለማድረግ ወይም ለአንድ ግዢ ለሚከናወንበት ጉዳይ ወይም በግዢ ህጉ መሰረት ለሚሰጥ ስራ ረቂቅ ስምምነት እንዲዘጋጅ ለሚቀርብ ጉዳይ የሚሰጥ አገልግሎት ሲሆን ከውሉ መፈረም አስቀድሞ በሚደረግ የውል ድርድር ተሳትፎ ለማድረግ የሚጠየቅ አገልግሎትን ይጨምራል፡፡
Legal Advices
ፍትህ ሚኒስቴር በሕግ ጉዳዮች የፌዴራል መንግስትን የማማከር ኃላፊነት በህግ ተሰጥቶታል። ይህን መነሻ በማድረግ ለመንግስት ተቋማት የህግ ምክር አገልግሎት ...በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን በረቂቅ ህግ ዝግጅት፣ በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ህግ ነክ ችግሮች እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ምክር/አስተያየት የሚሰጥበት ሂደት ነው። የህግ ምክር አገልግሎት ለማግኘት ምክር የሚፈለግበት ጉዳይ ዝርዝር እና የጉዳዩ አመጣጥ በአግባቡ ተብራርቶ፣ በተቋሙ የስራ ኃላፊ ተፈርሞ እና የተቋሙ ማህተም የተደረገበት ደብዳቤ መቅረብ አስፈላጊ ነው።
Alternative dispute resolution
የመንግሥት ተቋማት እርስ በርስ ወይም የመንግሥት ተቋማት ከግለሰቦች ወይም የግል ድርጅቶች የሚኖራቸውን ንግድ ነክና ፍትሐብሔር ...አለመግባባት በድርድር፣ በስምምነት፣ በዕርቅ ወይም በሌላ ከፍርድ ቤት ውጭ ባለ አማራጭ እንዲፈታ ለማድረግ ወይም አቅመ ደካማ የሆኑ ዜጎች አለመግባባታቸውን ከፍርድ ቤት ውጭ ባለ አማራጭ እንዲፈታላቸው የሚቀርብ አገልግሎት ሲሆን በድርድር፣ የግልግል ዳኝነትና የፍርድ ቤት ወይም ከፊል የዳኝነት አካል በተጀመረ ሂደት ላይ እገዛ እንዲደረግ የሚቀርብ ጉዳይ ን ያካትታል፡፡
Legal Drafting
ለፍትህ ሚኒስቴር በህግ ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል የሕግ ማርቀቅ ወይም የህግ ረቂቅ ማዘጋጀት አገልግሎት አንዱ ሲሆን በሕግ ጥናት፣ ማርቀቅ እና ማጠቃለል ...ዳሬክቶሬት ጄኔራል የሥራ ክፍል የሚከናወን ነው። የሚረቀቀውም ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ህግ (አዋጅ፣ ደንብ ወይም መመሪያ) ሊሆን ይችላል። በፍትሕ ሚኒስቴር ሕግ እንዲረቀቅላቸው የሚፈልጉ የመንግስት ተቋማት አገልግሎቱን ለማግኘት የሕግ ይረቀቅልኝ ጉዳይ ማቅረብ፣ በጉዳዩ ላይ የተዘጋጀ ፖሊሲ ሰነድ ካለ፣ በጉዳዩ ላይ የተደረገ የጥናት ሰነድ እንዲሁም ማሻሻያ ረቂቅ ህግ የሚዘጋጅ ከሆነ የሚሻሻለው ሕግ ቁጥር ወይም የሚረቀቀው ሕግ ደንብ ወይም መመሪያ ከሆነ እናት ሕጉ (ደንብ ወይም መመሪያውን እንዲወጣ ሥልጣን የሚሰጠው አዋጅ ቁጥር) ጠቅሶ ማሳወቅ እንደ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጠዋል።
Decision
የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ በርሳቸው ባልተግባቡበት የፍትሐብሔር ጉዳይ ላይ በአዋጅ ቁጥር 1263/2021 አንቀጽ 40(2)(ሀ) ...መሰረት ውሳኔ እንዲሰጥ የሚቀርብ ጉዳይ ነው፡፡
Legal Review
የህግ ማረም አገልግሎት በመንግስት ተቋማት የተዘጋጀውን ረቂቅ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ህግ (አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ) ከህገ መንግስቱ፣ ሀገራችን ከተቀበለቻቸው ...ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ ሌሎች ብሔራዊ ህጎች ጋር ተጣጥሞ የተዘጋጀ መሆኑን እና የህግ ማርቀቅ መርሆችን የተከተለ መሆኑን ለማረጋገጥ በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ስራ ክፍል የሚከናወን የረቂቅ ምርመራ እና አስተያየት ዝግጅት ስራ ነው። የህግ እርማት ጉዳይ ሲቀርብ በጉዳዩ ላይ የተዘጋጀ ፖሊሲ፣ በጉዳዩ ላይ የተደረገ መነሻ ጥናት፣ የረቂቅ ሕጉ የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቅጂ እንዲሁም የረቂቅ ህጉ ማብራሪያ በዎርድ ፎርማት በሶፍት ኮፒ እና በሃርድ ኮፒ ማቅረብ ከአገልግሎት ጠያቂው የመንግስት ተቋም ይጠበቃል።
International Cases
የፌዴራል መንግሥት ወይም ተቋማት በውጭ ሀገር የገጠማቸውን ክስ ወይም ንግድ ነክ አለመግባባት አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥ ወይም ድርድር ...ላይ ተሳትፎ እንዲደረግ ወይም በዳኝነት አካላት ክርክር እንዲደረግ ወይም ማናቸውም ከአለም አቀፍ ፍትሐብሄር ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተቋማት የሚቀርብ የድጋፍ ጉዳይ ነው፡፡
Registrations
መመሪያ ሕግ አውጪው አካል በሚሰጠው የውክልና ስልጣን መሰረት በአስተዳደር ተቋም የሚወጣና የተቋሙን ስራ ለማቀላጠፍ የሚያስችል የሕግ ሰነድ ነው። ...የሚዘጋጀው መመሪያ አዲስ፣ በስራ ላይ ያለ መመሪያን የሚያሻሻል ወይም የሚሽር ሊሆን ይችላል። በአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 መሰረት ፍትህ ሚኒስቴር በመንግስት ተቋማት የሚዘጋጁ መመሪያዎችን መዝግቦ ቁጥር በመስጠት ለተደራሽነት በመስሪያ ቤቱ ድረ ገፅ ላይ የመጫን ኃላፊነት ተሰጥቶታል። በተቋማት የሚዘጋጁ መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ከሕዝብ እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ፣ ረቂቅ መመሪያውን ለፍትህ ሚኒስቴር አቅርቦ አስተያየት እንዲሰጥበት ማድረግ ይጠበቃል። ይህን ሂደት አልፎ ለምዝገባ የሚላክ መመሪያ በተደረጉት ውይይቶች እና በተሰጡት አስተያየቶች መሰረት ማስተካከያ የተደረገበት እና የአርትኦት ስራ የተሰራበት፣ መመሪያው በአማርኛ እና በኢንግሊዝኛ ቅጂ የተዘጋጀ፣ የመመሪያው ማብራሪያ፣ መመሪያው በአዘጋጅ ተቋሙ በሚመለከተው አካል (ስራ አመራር) የፀደቀ መሆኑን የሚያሳይ ደብዳቤ ተያይዞ መቅረብ አለበት። እነዚህ ሰነዶች በሀርድ ኮፒ እና በሶፍት ኮፒ (በሲዲ) መላክ አለባቸው።
Litigation and Representation
የፌዴራል የመንግስት ተቋማት ወይም የገንዘብ አቅም የሌላቸው ዜጎች የገጠማቸውን የፍትሐብሔር ወይም ንግድ ነክ የመብትና ጥቅም ጉዳይ በተለይ ለፌዴራል ...ፍርድ ቤት ወይም ለሌላ የዳኝነት አካል ክስ አቤቱታ እንዲቀርብ፣ ለአቤቱታዎች ምላሽ እንዲሰጥ፣ ወይም እግድና ይግባኝ እንዲቀርብ እንደ አግባብነቱ በጋራ ወይም በተናጠል ክርክር ለማድረግ የሚጠየቅ አገልግሎት ነው፡፡
Inspection and Followup
ሁሉም የመንግስት ተቋማት የሚገቡትን ውል እና የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ተፈጥሮ ምንም ይሁን ምን መረጃ እንዲሰጡ በሕግ ይገደዳሉ። ስለዚህ ጉዳያቸው ምን ያህል ...እንደሆነ ለማወቅና የህዝብን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ በተቋማቱ በአግባቡ እየተስተናገዱ መሆኑን ለመፈተሽ ሲኢአድጂ የመንግስት ተቋማትን በአካል ይጎበኛል። በግኝቶቹ መሰረት፣ CJADG ምክሮችን ይሰጣል እና የውሳኔ ሃሳቦቹን አፈፃፀም ይከታተላል። የመረጣቸውን ጉዳዮች በቀጥታ በማስተናገድ ላይም ይሠራል።
Recomendations
መመሪያ ሕግ አውጪው አካል በሚሰጠው የውክልና ስልጣን መሰረት በአስተዳደር ተቋም የሚወጣና የተቋሙን ስራ ለማቀላጠፍ የሚያስችል የሕግ ሰነድ ነው። የሚዘጋጀው ...መመሪያ አዲስ፣ በስራ ላይ ያለ መመሪያን የሚያሻሻል ወይም የሚሽር ሊሆን ይችላል። በአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 መሰረት ፍትህ ሚኒስቴር በመንግስት ተቋማት የሚዘጋጁ መመሪያዎችን መዝግቦ ቁጥር በመስጠት ለተደራሽነት በመስሪያ ቤቱ ድረ ገፅ ላይ የመጫን ኃላፊነት ተሰጥቶታል። በተቋማት የሚዘጋጁ መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ከሕዝብ እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ፣ ረቂቅ መመሪያውን ለፍትህ ሚኒስቴር አቅርቦ አስተያየት እንዲሰጥበት ማድረግ ይጠበቃል። ይህን ሂደት አልፎ ለምዝገባ የሚላክ መመሪያ በተደረጉት ውይይቶች እና በተሰጡት አስተያየቶች መሰረት ማስተካከያ የተደረገበት እና የአርትኦት ስራ የተሰራበት፣ መመሪያው በአማርኛ እና በኢንግሊዝኛ ቅጂ የተዘጋጀ፣ የመመሪያው ማብራሪያ፣ መመሪያው በአዘጋጅ ተቋሙ በሚመለከተው አካል (ስራ አመራር) የፀደቀ መሆኑን የሚያሳይ ደብዳቤ ተያይዞ መቅረብ አለበት። እነዚህ ሰነዶች በሀርድ ኮፒ እና በሶፍት ኮፒ (በሲዲ) መላክ አለባቸው።
"For law, justice, Equity"
Contact Us
Our Address
Bambis, Jomo Kenyatta Avenue, Addis Ababa, Ethiopia
Email Us
info@moj.gov.et
Call Us
011 551 5099
